Fana: At a Speed of Life!

ከካራቆሬ – ከሚሴ ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከካራቆሬ – ከሚሴ ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮቹንና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ከሥርጭት ኔትወርክ መስመሮች ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ በርብርብ ሲሰራ ቆይቶ ነው ዛሬ እስከ ከሚሴ ድረስ ያሉት ከተሞች ኃይል ማግኘት የቻሉት፡፡

ከደብረብርሃን ኮምቦልቻ ድረስ ያሉት ከተሞች በ132 እና በ230 ኪሎ ቮልት መስመሮች ኃይል ያገኙ የነበረ ቢሆንም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው የተባለው።

ይሁንና የኃይል ተጠቃሚው ህብረተሰብ በፍጥነት ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግም ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር ለጊዜው በማቆየትና ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመሩን በአስቸኳይ በመጠገን ዛሬ እስከ ከሚሴ ድረስ ያሉት ከተሞች ኃይል አግኝተዋል።

የጥገና ሥራው ወደ ደሴ ከተማ ቀጥሎ እስከ ሀርቡ ባለው አካባቢ መስመሮችን የመጠገን ሥራም እየተካሄደ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አሁን አስቸኳይ ጥገና እየተደረገለት ያለው 132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የከሚሴ፣ ኮምቦልቻ እና ደሴ እንዲሁም ዓለም ከተማና በምዕራብ አፋር የሚገኙ ከተሞችን ኃይል እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው፡፡

በተመሳሳይ በሚሌ ባቲ ያለው መስመር ላይ ሁለት ኃይል ተሸካሚ ምሶሶዎች በከባድ መሳሪያ በመመታታቸውና ጉዳቱ ከባድ በመሆኑ ምሶሶዎቹን እንደገና የመትከል ስራ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.