Fana: At a Speed of Life!

የወጣቶች የጤና መረጃ እና ክህሎት ማስፋፊያ መተግበሪያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ጤና መረጃ እና ክህሎት ለማስፋፋት የሚያገለግል “የኔታብ” የተሰኘ የእጅ ስልክ መተግበሪያ ይፋ አደረገ።
በጤና ሚኒስቴር የእናቶች እና የህፃናት ጤና እና የስነ ምግብ ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት ዘላለም መተግበሪያውን ይፋ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት፥ ቴክኖሎጂው ከ14 እስከ 25 የእድሜ ክልል ለሚገኙ አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች በ6 የአገር ውስጥ እና የውጭ ቋንቋዎች አገልግሎት ይሰጣል።
አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ አፋርኛ፣ ሶማሊኛ፣ ትግሪኛ እና እንግሊዘኛ መተግበሪያው አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቋንቋዎች መሆናቸውንም አብራርተዋል።
መተግበሪያው አካልን ለመረዳት፣ መልካም ጓደኝነትን ለመመስረት፣ የስነ ተዋልዶ ጤና ክህሎትን ለማዳበር፣ የሱስና እና የሱሰኝነት ተጋላጭነትን ለመቋቋም፣ ስርአተ ምግብን ለማሻሻል እና የህይወት ክህሎትን ለማዳበር የሚያስችሉ ስድስት ቁልፍ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥም ነው ዶ/ር መሰረት ያስረዱት።
መተግበሪያው ጤና ሚኒስቴር በ 952 ነጻ የስልክ መስመር የሚሰጣቸውን የጤና ነክ የምክር አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት እንደሚረዳም ገልፀዋል።
መተግበሪያውን የጤና ሚኒስቴር ከመንግስታቱ ድርጅት የስነ ህዝብ ጽ/ ቤት እና የኢትዮጵያ የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ማህበር ጋር በመተባበር ነው ያበለጸገው።
በወንድወሰን አረጋኸኝ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.