የሀገር ውስጥ ዜና

በሶማሌ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ለመሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሰጥ ተገለጸ

By Meseret Awoke

December 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድና ምክትላቸው ኢብራሂም ኡስማን የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በኩርፋሳዋ ቀበሌ የሚገኙ ተፈናቀይ ዜጎችን ገበኙ፡፡

ልዑካን ቡድኑ ከአሁን በፊት መንግስት በሲቲ ዞን መኤሶ ወረዳ ሙሊ ከተማ ላይ የመጠለያ ጣቢያ የሰራላቸው ተፈናቃይ ዜጎችን ኑሮ ለመመልከት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በዚህም መንግሥት ለተፈናቃዮችና ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ለመሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሰጥ መግለጻቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ የሚመራው ልዑክ ተፈናቃዮቹ በአሸባሪው ህወሓት ስልጣን ዘመን ከኦሮሚያ ክልል መኢሶ ወረዳ በሁለቱ ወንድማማች ኦሮሞና ሶማሌ ህዝቦች መካከል የቀሰቀሰውን ግጭት ሳቢያ ተከትሎ ከቀያቸው የተፈናቀሉ መሆናቸው ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!