የሀገር ውስጥ ዜና

ባቲ፣ አቀስታ፣ መሀል ሳይንት እና ሳይንት አጅባር ከተሞች ኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ

By Meseret Awoke

December 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባቲ፣ አቀስታ፣ መሀል ሳይንት እና ሳይንት አጅባር ከተሞች ኤሌክትሪክ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡

ወራሪው የህወሓት ቡድን ባደረሰው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጉዳት ምክንያት የተጎዱ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች የመጠገንና መልሶ የማገናኘት ስራው ተጠናክሮ እየተሰራ እንደሚገኝ የኤሌክተሪክ አገልግሎት ገልጿል፡፡

የሰራተኞችና ማኔጅመንት አባላት እያደረጉ ባለው በሰዓት ያልተገደበ ተግባር ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸው የነበሩ ከተሞች ኤሌክትሪክ መልሰው እያገኙ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት ጠዋት ማጀቴ ከተማ ኃይል ያገኘች ሲሆን ÷ ከሰዓት በኋላ ባቲ፣ አቀስታ፣ መሀል ሳይንት እና ሳይንት አጅባር ከተሞች ኤሌክትሪክ የተገናኘላቸው መሆኑን የደሴ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አበበ አሳውቀዋል፡፡

በደሴ ዲስትሪክት ስር አገልግሎት የሚያገኙት ከሚሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ እና ጨፋ ሮቢት ከተሞች ኤሌክትሪክ ማግኘታቸውን ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!