የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ትዝታ በኔፓል የሚገኙ የአፍሪካ የክብር ቆንሥላዎችን አህጉሪቷን እንዲያስተዋውቁ እና በአፍሪካ የንግድ ትሥሥር መፍጠር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ እንዲሰሩ ጠየቁ

By Meseret Awoke

December 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ በኔፓል የአፍሪካ የክብር ቆንሥላዎችን አግኝተው አፍሪካን ለኔፓል ህዝቦች ማስተዋወቅ እና በኔፓልና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ትብብር መመሥረት በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደሯ አፍሪካ በአንዳንድ የውጪ መገናኛ ብዙኃን ጨለማ አህጉር ተብላ እየተሳለች እንደቆየች ገልጸው እኛ አፍሪካውያን ግን አህጉሯ በወጣቶች የተሞላችና ብሩህ ተሥፋ ያላት መሆኗን ማሳየት ይጠበቅብናልም ብለዋል፡፡

አፍሪካውያን በሀገራቸው የውስጥ ጉዳይ ላይ ለሚፈጸም የውጪ ጣልቃ ገብነትና አፍራሽ ፍላጎትም “በቃ” ማለታቸውን ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ የክብር ቆንሥላዎችም አምባሳደሯ አፍሪካን ከፍ በማድረጋቸው አመስግነው አህጉሪቷን ለኔፓል ዜጎች ለማስተዋወቅ በቅንጅት እንደሚሰሩ ገለጸዋል፡፡

በቀጣይም በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን ያሳተፈ የመረጃ ልውውጥ እና ውይይት መርሃ ግብር ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን ጠቁመዋል፡፡

በአፍሪካ ውስጥ በሚከናወኑ የሰብዓዊ ድጋፎች ላይም ለመሳተፍ ቃል ገብተዋል፡፡

በአፍሪካ ሀገራት እና በኔፓል መካከል የንግድና እና የቱሪዝም ትስስር በሚፈጠርበት ሁኔታ ላይ እንሠራለን ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!