ቢዝነስ

በእሁድ ገበያ ከ48 ሚሊየን ብር በላይ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ግብይት ተፈፅሟል – የመዲናዋ ህብረት ስራ ኤጀንሲ

By Feven Bishaw

December 12, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በእሁድ ገበያ ከ48 ሚሊየን ብር በላይ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ግብይት መፈጸሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

7ኛ ሳምንቱን በያዘው የእሁድ ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለህብረተሰቡ ማቅረቡን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡