የሀገር ውስጥ ዜና

ተንታ፣ ማሻና ወግዲ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሃይል አገኙ

By Meseret Awoke

December 13, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተንታ፣ ማሻና ወግዲ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት በድጋሚ ማግኘታቸውን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የወደመባቸውን ከተሞች የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመሮችንና ምሰሶዎችን በመጠገን ነፃ የወጡ ከተሞችን ከስር ከስር እተከተለ የኤሌክትሪክ ኃይል መልሶ የማገናኘት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡

በዚህም ተንታ፣ ማሻና ወግዲ ከተሞች የሚያገኙበትን የመካከለኛና የዝቅተኛ መስመር ጥገና በማጠናቀቅ አገልግሎቱን ትላንትና ዛሬ ጠዋት እንዲያገኙ መደረጉን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!