የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

December 14, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ጸሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየው ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም የሶማሌ ክልል ከዚህ ቀደም አለመረጋጋት የሚስተዋልበት ክልል እንደነበር ዶክተር ወርቅነህ አስታውሰዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ችግሩ መቀረፉን የገለጹት ዋና ጸሃፊው ÷ ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ያላቸውን አድናቆትም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ሊሰሩባቸው በሚችሉ መንገዶች ላይ መምከራቸውን ዶክተር ወርቅነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የተመራው ልዑክ ሄሪቴጅ ኢንስቲትዩት በተባለው ዓለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ተቋም በተዘጋጀና ቀጠናዊ አጀንዳዎች ላይ በመከረ መድረክ ላይ ለመሳተፍ ነበር ወደ ጂቡቲ ያቀናው።

በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የተመራው ልዑክ ሄሪቴጅ ኢንስቲትዩት በተባለው ዓለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ተቋም በተዘጋጀና ቀጠናዊ አጀንዳዎች ላይ በመከረ መድረክ ላይ ለመሳተፍ ነበር ወደ ጂቡቲ ያቀናው።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!