የሀገር ውስጥ ዜና

ፊንላንድ ለኢትዮጵያ 4 ነጥብ 1 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች

By Meseret Awoke

December 14, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊንላንድ በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች 4 ነጥብ 1 ሚሊየን ዩሮ የሰብዓዊ ድጋፍ ለዓለም የምግብ ፕሮግራም ኢትዮጵያ እንደምታበረክት አስታውቃለች።

ፊንላንድ በኢትዮጵያ የድርጅቱን የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ለመደገፍ የ1 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጻለች።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለገንዘብ ድጋፉ አመስግኖ፥ ድጋፉ ህይወት አድን እንደሚሆን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አመልክቷል።

በሌላ በኩል ስዊድን እና ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ በግጭቱ የተጎዱ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሰረት ስዊድን በ1 ነጥብ 23 ሚሊየን ዩሮ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ከ23 ሺህ በላይ የአማራ ክልል ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ማቀዷም ነው የተገለጸው።

ስዊድን ከአጋር ድርጅቱ ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን በትግራይ፣ አፋር እና ጋምቤላ ክልሎች ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ እያደረገች መሆኑን በኢትዮጵያ ከሚገኘው ስዊድን ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!