የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በደቡብ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ለዘላቂ ልማት ኮሚሽን አባል እንድትሆን ጥሪ ቀረበላት

By Tibebu Kebede

February 14, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በደቡብ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ለዘላቂ ልማት ኮሚሽን አባል እንድትሆን ጥሪ ቀረበላት።

በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አስጋር አሊ ጎሎ ፓኪስታንና ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፣ በሰው ሀብት ልማት፣ በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እንዲሁም በኢንዱስትሪ ልማት በጋራ መስራት በሚችሉበት አግባብ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብረሃም በላይ ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደሩ ዶክተር አብረሀም በላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው እንኳን ደስ አለዎት ብለዋቸዋል።

አያይዘውም ሚኒስትሩ በፓኪስታን እየተሰሩ ያሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንዲጎበኙ ጋብዘዋቸዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ 27 ሃገራትን በአባልነት በሚያሳትፈው የደቡብ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ለዘላቂ ልማት ኮሚሽን አባል እንድትሆን አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ሚኒስትሩም የተደረገላቸውን ግብዣ በመቀበል ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር በተለያዩ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መስኮች በጋራ ለመስራት ፈቃደኛ ናት ማለታቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision