Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት ከኮምቦልቻ እስከ ሰመራ ባለው ማስተላለፊያ መስመር ላይ 52 ሚሊየን ብር የሚገመት ውደመት አድርሷል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት ከኮምቦልቻ እስከ ሰመራ ባለው ማስተላለፊያ መስመር ላይ 52 ሚሊየን ብር የሚገመት ውደመት ማድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታወቀ፡፡

የአሸባሪው ህወሃት ቡድን በአፋርና በአማራ ክልል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች የህዝብና የመንግስት መገልገያ መሰረተ ልማቶችን፣ ተቋማትና ድርጅቶችን እንዲሁም የግለሰብ ሃብትና ንብረት በመዝረፍና በማውደም ጸረ-ህዝብ መሆኑን በተግባር አሳይቷል፡፡

ከኮምቦልቻ ወደ ሰመራ የሚሄደው ከፍተኛ ኃይል ተሸካሚና አስተላላፊ የኤሌክትሪክ ሳይት ደግሞ በሽብር ቡድኑ ከፍተኛ ውድመት ከደረሰባቸው መሰረተ ልማቶች አንዱ ነው፡፡

ይህም በሰመራና በተለያዩ የአፋር ክልል ከተሞች በሚኖሩ ዜጎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ላይ ለወራት የዘለቀ አሉታዊ ጫና አሳድሮ ቆይቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የትራንስሚሽን ኦፕሬሽን ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ አቶ ኃብታሙ ውቤ፥ አሸባሪው ህወሓት ወራሪ ኃይል ውድመት ያደረሰባቸው ከደብረሲና እስከ ደሴ ድረስ የሚገኙ መስመሮች በመጀመሪያ ምዕራፍ ጥገና እንደተካሄደላቸው ገልጸዋል፡፡

ሁለት ኃይል ተሸካሚ ታወር እና ኃይል አስተላላፊ ኮንዳክተሮች ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን አሁን ላይ ከኮምቦልቻ ሰመራ ያለው ኤሌክትሪክ ሳይት ጥገና ከ60 በመቶ በላይ መጠናቀቁን አመላክተዋል፡፡

ውድመት የደረሰባቸው ጥሬ ዕቃዎች የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቁ ቢሆንም የቅድመ ዝግጅት ስራው ፈጥኖ በመከናወኑ ወደ ጥገና ስራ መግባት እንደተቻለ ጠቁመዋል፡፡

ከ150 በላይ ሰራተኞችን በመመደብ ጥገናውን በተያዘው ሳምንት መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቀጣይም ከሽብር ቡድኑ ወራሪ ኃይል ነፃ በሆኑ አካባቢዎች ፈጣን የጥገና ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.