Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሽብርተኛው የህወሓት ወራሪ ኃይል ለተፈናቀሉ የአፋር ክልል ወገኖች የሚውል የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሽፈራው ተሊላ÷ በአፋርና አማራ ክልሎች በወራሪውና ሽብርተኛው የህወሓት ኃይል ውድመት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ መስመሮች በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

61 ሚሊየን ብር ገንዘብ ሽብርተኛውን የህወሓት ወራሪ ኃይል እየተፋለመ ለሚገኘው ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በማድረግ ተቋሙ ደጀን መሆኑን እንዳሳየ አስታውሰዋል።

በዛሬው ዕለትም ተቋማቸው ለአፋር ክልል ወገኖች የሚውል የሶስት ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ነው የተናገሩት።

የክልሉን ሁለንተናዊ ልማት ለማሳለጥም የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታው እየተቀላጠፈ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በበኩላቸው÷ ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ካለው ከንቱ ቅዠት የተነሳ በአማራና አፋር ክልሎች መጠነ ሰፊ ወረራ በማድረግ ዜጎችን ማጎሳቆሉን ገልጸዋል።

የሽብር ቡድኑ ይዞት የመጣውን ወራሪ ኃይል ከአፋር እንዳይወጣ ለማድረግ የአፋር ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ቅንጅት ፈጥረው አንጸባራቂ ድል አስመዝግቧል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.