የሀገር ውስጥ ዜና

ላለፉት 27 አመታት በሶማሌ ክልል የደረሰው ችግርና ጭቆና ዳግም አይመለስም – አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ

By Meseret Awoke

December 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የሶማሌ ክልል ተወላጅ የዳያስፖራ አባላት አገር ለማዳን በሚደረገው እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጎን መሆናቸውን ገለጹ።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዳያስፖራ ለአገራቸው ሉዓላዊነት ህልውና ላደረጉት ድጋፍ በስልክ ባስተላለፉት መልእክት ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ላለፉት 27 አመታት በሶማሌ ክልል የደረሰው ችግርና ጭቆና ዳግም አይመለስም ብለዋል።

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የሶማሌ ክልል የዳያስፖራ አባላት በአገራቸው ኢትዮጵያ እና በሶማሌ ክልል የሰፈነው አስተማማኝ ሰላም እና ለውጥ እንዲጠናከር የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልፀዋል።

የዳያስፖራ አባላቱ ከመንግስት ጎን ነን ማለታቸውን ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በሌላ በኩል የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ የሶማሌ ክልል ዳያስፖራ አባላት ምስጋና አቅርቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!