Fana: At a Speed of Life!

የተቀናጁ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ማጠናከር የሚያስችል የ2 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጀክት ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጋር በኢትዮጵያ ዘላቂ የተቀናጁ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
 
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሠረተ ልማትና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ÷ስምምነቱ የተጠናከረ የተቀናጁ አግሮ ኢንዱስትሪያል ፓርኮችን ለማጠናከር የሚያስችል በመሆኑ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
 
የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዋና ዳይሬክተር ኦሪሊያ ማትሪዚያ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ የተቀናጁ አግሮ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ልማት ለማጠናከር የሚያስችል ፕሮጀክት ለ3 ዓመታት በጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ሁለት ሚሊየን ዩሮ ለጋሽነት የሚከናወን መሆኑን ጠቁመዋል።
 
የተቀናጁ የአግሮ ኢንዱስትሪ ስኬት በአብዛኛው የተመካው በፓርኮች ውስጥ የሚቋቋሙትን ኢንዱስትሪዎች ለመመገብ የግብርና ምርቶች የእሴት ሰንሰለቶች በበቂ ዝግጁነት እና የፓርኩን ትክክለኛ አስተዳደር አሰራር ላይ ያተኮረ ነው ማለታቸውንም ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
የአነስተኛ ይዞታ እርሻዎችን፣ የአነስተኛ ደረጃ ማቀነባበሪያ ኢንተርፕራይዞችን እና አጋር ኢንዱስትሪዎችን ከንግድ እሴት ሰንሰለቶች ጋር ማቀናጀት፣ አስተማማኝ የምግብ ደህንነት ሥርዓት መዘርጋት፣ በፓርኮች ውስጥ ፍትሃዊ የሰው ኃይል ግንኙነቶችን ማስተዋወቅ ለስኬታማነቱ የሚስፈልጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.