Fana: At a Speed of Life!

የአሰላ ፋና ኤፍ ኤም ሰራተኞች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሰላ ፋና ኤፍ ኤም ሰራተኞች ከአሰላ ከተማ ጢዮ ወረዳ እና አርሲ ዞን ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር በመሆን የዘማች ቤተሰቦችን የደረሰ ሰብል ሰብስበዋል፡፡
የሰብል ስብሰባው ተሳታፊዎች ለሀገር ህልውና መስዕዋት እየከፈሉ ከሚገኙ የመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ቤተሰብ ጎን መሆናችንን በተግባር ለማሳየት ነው የተገኘነው ብለዋል፡፡
ለህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ከመስጠት ባለፈ ለመከላከያ ሰራዊት ደጀንነታቸውን ለማሳየት ድጋፍ ማድረጋቸዉን ተናግረዋል፤ ሀገር በምትፈልጋቸው ሁሉ ምላሽ እንደሚሰጡም አንስተዋል።
ሰብል የተሰበሰበላቸው የዘማች ቤተሰቦች በበኩላቸው፥ ሰብሉ በወገን ትብብር በወቅቱ በመሰብሰቡ ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የአሰላ ፋና ኤፍ ኤም 90 ነጥብ 0 የፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ ዮናታን ብርሃኑ÷ መረዳዳት የኢትዮጵያ ውያን እሴት በመሆኑ የዘማች ቤተሰቦችን በጉልበትና በገንዘብ የመደገፍ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡
በኦሊያድ በዳኔ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.