Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ከኔቶ መስፋፋት ጋር በተያያዘ ከምዕራቡ ዓለም ጋር አስቸኳይ ውይይት እንደምትፈልግ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳንድ ድርጅት /ኔቶ/ መስፋፋት ጋር በተያያዘ ከምእራባውያኑ ጋር አስቸኳይ ውይይት ማድረግ እንደምትፈልግ አስታወቀች።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከዩክሬን ጋር በምትዋሰንበት ድንበር ላይ የተፈጠረውን ውጥረት አስመልክቶ የሞስኮን የደህንነት ችግር አደጋ ላይ እንዳይጥል የሚያስችል ዋስትና ለማግኘት ከአሜሪካ እና ከኔቶ ጋር በአስቸኳይ መነጋገር እፈልጋለሁ ብለዋል ፡፡

በሞስኮ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል በዩክሬን ጉዳይ ላይ ውጥረቱ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ፕሬዚዳንት ፑቲን ከአሜሪካ እና ከኔቶ ጋር በፀጥታ ዋስትና ላይ አፋጣኝ ውይይት እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ነው ዘገባው የሚያስረዳው ።

ፕሬዚዳንት ፑቲን ትናንት ማክሰኞ ሩሲያ እና ምእራባዊያን መካከል በተለምዶ እንደአደራዳሪ ከምትቆጠረው ፊላንድ ፕሬዜዳንት ሳውሊ ኒንስስቶ ጋር በስልክ እንደተነጋገሩና ሀገራቸው የጸጥታ እና የደህንነት ጉዳይ ላይ በምትፈልገው ዋስትና ላይ ከአሜሪካ እና ከኔቶ አስቸኳይ ውይይት እንደሚፈልጉ እንደነገሯቸው ተመልክቷል።

የሩሲያ ጥያቄ ኔቶ በምስራቅ በኩል መስፋፋቱን እና ዩክሬንን ጨምሮ በአጎራባች ግዛቶች የጦር መሳሪያ ማከማቸቱን እንዲያቆም ማድረግ እንደሆነ ፕሬዝዳንቱ መናገራቸውን ዘገባው አስፍሯል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፕሬዚዳንት ፑቲን ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በተመሳሳይ ጉዳይ የስልክ ልውውጥ እንዳደረጉ ተጠቆሟል፡፡

ውጥረቱን ተከትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የሩስያ ወታደሮች በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ መስፈራቸውን ቲአርቲ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.