Fana: At a Speed of Life!

በጥቁር ገበያ የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የሚያደርግ አሠራር መዘርጋቱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥቁር ገበያ የተሰማሩ አካላትን ከፍትህ አካላት ጋር በመተባበር ተጠያቂ የሚያደርግ አሠራር መዘርጋቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አመራሮች ጋር በቀጣይ አብረው በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ሰሎሞን ሶካ ኮሚቴው በፋይናንስ ተቋማት ተደራሽነት፣ በውጭ ምንዛሬ እና በጥቁር ገበያ ተግዳሮት፣ በኦዲት ግኝት እንዲሁም የሕዝብ ቅሬታ የሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተል ገልጸዋል፡፡
ብሔራዊ ባንኩ የዋጋ ንረት ከማረጋጋት፣ የብሔራዊ ባንክ ህጎችን የሚጥሱ ባንኮች የቁጥጥር ሥራ፣ በጦርነቱ የወደሙ ባንኮችን መልሶ የማቋቋም ሥራ፣ የብድር አገልግሎት በተለይ ግብርና ዘርፍ ላይ ችግሩን ለመቅረፍ ባንኩ በቀጣይ የተያዙ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ ጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት ያላቸው በተለይ በግብርናው ዘርፍ ላይ ድጋፍ በመስጠት ብድር መበደር እንዲችሉ በቅርቡ የወጣውን አዋጅ ተግባራዊ በማድረግ ችግሩ እንደሚቀረፍ ገልጸዋል።
በሸሪያ ባንክ ህግ የሚመሩ ባንኮች ደግሞ ራሳቸውን ችለው እንዲቋቋሙ እና የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ለማዘመን የሪፎርም ሥራ እየሠሩ ነው ማለታቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል።
በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ባንኮች እና ቅርንጫፎች ላይ እንደ አዲስ ጥሬ ገንዘብ ኦዲት በማድረግ አገልግሎት እንዲሰጡ መልእክት ማስተላለፋቸውን የገለጹት የባንኩ ገዥ የብሔራዊ ባንክ ህግ በሚጥሱ ባንኮች አስተማሪ የሆነ ቅጣት እንደተቀጡ አብራርተዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.