Fana: At a Speed of Life!

ሃገር ወዳድ አትሌቶች  ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፋቸው ታላቅ ኩራት እንደፈጠረላቸው ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃገር ወዳድ አትሌቶች ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፋቸው ታላቅ ኩራት እንደፈጠረላቸው ተናገሩ።

አትሌት ገዛኸኝ አበራ ፣ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ እና አትሌት ኮማንደር ማርቆስ ገነቴ ከዚህ በፊት በሩጫው አለም የሃገራቸውን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ የቆዩ ናቸው።

እነዚህ አትሌቶች ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሰለፍ ጠላትን ድባቅ መምታታቸውን መናገራቸውን ነው ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለከተ፡፡

“የሰራዊታችን የጀግንነት ታሪክ ብናውቀውም ግንባር ከደረስን በኋላ ያየነው ጀግንነት ግን እጅን አፍ ላይ የሚያስጭን ተግባር ነው”  ብለዋል አትሌቶቹ፡፡

በአሁኑ ሰአት ጠላትን መውጫ መግቢያ እያሳጣው ከሚገኘው ሰራዊት ጎን ተሰልፈው መቆማቸውን እና ይህን ጨካኝ እና አረመኔ ቡድን ከእነተንኮልና ሴራው እስከ ወዲያኛው ለመቅበር እስከ መጨረሻው ደረስ በፅናት ቆመው አስፈላጊውን የአካል እና የህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.