Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 5 ወራት ከቆዳ ኢንዱስትሪ የወጪ ንግድ 19 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ያለፉት አምስት ወራት ከቆዳ ኢንዱስትሪ የወጪ ንግድ 19 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ የበጀት ዓመቱን አምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እና በቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፉን ችግሮች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳኛቸው ሽፈራው እንደገለጹት÷ በበጀት ዓመቱ አምስት ወራት ከዘርፉ 26 ሚሊዮን 815 ሺህ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል።

በዚሁ መሰረት 19 ሚሊየን ዶላር ገቢ ወይንም የዕቅዱን 70 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ነው የገለጹት።

ኢትዮጵያ ከአጎዋ የንግድ ሥርዓት መውጣቷን ተከትሎ ሊያጋጥማት የሚችለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት መተካት የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

የአገሪቷ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ተደራሽ የሚሆኑባቸውን አማራጭ አገራት ማስፋት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውንም ጠቁመዋል።

ይህም በተለይ በአውሮፓ፣ በእስያ እና በአፍሪካ አገራት ገበያ ውስጥ ለመሳተፍና ተደራሽነትን ለማስፋት ከሚመለከታቸው አካላትና ተቋማት ጋር እየተሰራ ነው ብለዋል።

በአገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች ለአብነትም በደቡብ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ምዕራብ ክልሎች የበሬ ቆዳ በኮንትሮባንድ እየወጣ መሆኑንም ተናግረዋል።

በምስራቅ ኦሮሚያና በምስራቅ ሶማሌ እንዲሁም በምዕራብ ኦሮሚያ ጉጂና ቦረና አካባቢዎችም በተመሳሳይ በኮንትሮባንድ እንዲወጣ እየተደረገ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዚህ ሳቢያ በፋብሪካዎች ላይ እጥረት እያጋጠመና አገሪቷም ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እያጣች መሆኑን ገልጸዋል።

አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ እንዲህ አይነት ህገ-ወጥ ተግባር ላይ መሳተፍ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት በመረዳት የድርጊቱ ፈጻሚዎች እንዲታረሙም አሳስበዋል።

በ2014 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ከቆዳ ኢንደስትሪው 90 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ ስለመሆኑ የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመላክታል።

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.