Fana: At a Speed of Life!

ከ13 ሚሊየን በላይ ለሆኑ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ ነው – የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር

አዲስ አበበ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት በመላ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ከ13 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ለሆኑ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ እያቀረበ መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር አይድሩስ ሃሰን አስታወቁ።
ከመንግሥት ድጋፍ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድርጅቶች ለተለያዩ ክልሎች ድጋፍ እያቀረቡ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡
በዚህም በአፋር፣ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች እንዲሁም ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች፣ መድኃኒትና የተለያዩ ድጋፎች በመንግሥት ተደርጓል።
ኮሚሽኑም ድጋፎቹን በማድረስ፣ ባለሙያዎችን በማሰማራት፣ ማዕከላትን በማቋቋም ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ነው ያብራሩት፡፡
በትግራይ ክልል የሚቀርበው ድጋፍ በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድርጅቶች ቅንጅትና በዓለም ምግብ ፕሮግራም በኩል እየደረሰ ሲሆን፥ መንግሥትም ድጋፉን እያስተባበረ ነው ብለዋል፡፡
መንግሥት እያካሄደ ያለውን ዘመቻ ተከትሎ ከወራሪው ቡድን ነጻ በወጡ የአማራና አፋር ክልሎች ላይ ተጨማሪ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች መኖራቸውን አስታውቀዋል።
ተጨማሪ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ታሳቢ ባደረገ መልኩ በፌዴራል ደረጃ ከታኀሳስ እስከ ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ድረስ ከ40 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ በእቅድ መያዙንም አስረድተዋል፡፡
ለቀጣዮቹ ሰባት ወራት የተያዘው እቅድ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር እና ሁኔታ እየታየ ሊከለስ እንደሚችልም አቶ አይድሩስ ጠቁመዋል።
ለዚህም የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት አስተዋጽዎ እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።
ኮሚሽኑ በሚያደርገው የሰብዓዊ ድጋፍ በርካቶች ከአገር ውስጥ እና ከውጭ አገራት ገንዘብ እያሰባሰቡ መሆኑን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ÷ በተለይም በአይዞን ኢትዮጵያ በኩል ዳያስፖራው ማኅበረሰብ የሶስት ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.