Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ ኢትዮጵያን “በዘር ተኮር ጭፍጨፋ” ለመጠየቅ ታስቦ የነበረው ህግ ተሰረዘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን በዘር ተኮር ጭፍጨፋ ለመጠየቅ ታስቦ የነበረው ህግ መሰረዙ ይፋ ተደረገ፡፡

የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ከከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ያደረገውን ስብሰባ መሰረት በማድረግ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ለምክር ቤቱ መረጃ መላኩ ታውቋል፡፡

በመረጃውም በኢትዮጵያ “የዘር ተኮር ጭፍጨፋ ተካሂዷል” በሚል ሀሰተኛ ውንጀላ ኢትዮጵያን ለመጠየቅ የሚረዳና በአሜሪካ ሴኔት ቢሮ የታሰበው ሕግ ማለትም ÷ #HR_4350 አንቀፅ_6464_ “Determination of Potential Genocide or Crimes Against Humanity” የሚለው ረቂቅ ህግ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን ምክር ቤቱ ይፋ አድርጎል።

ታስቦ የነበረውን ህግ ለማሰረዝ በሴናተር ጂም እና በሲቪል ምክር ቤቱ መካከል አጀንዳ ሆኖ ክርክር ተደርጎበት ነበር።

የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ፕሬዚደንት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ለሴናተር ጂም ኢንሆፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማሳደር ሲል የፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር እየተከተላቸው ከነበሩት መንገዶች መካከል ይህ የተለያዩ ሚዲያዎችን የሀሰት መረጃ መሰረት አድርጎ ሲዘጋጅ የነበረው ህግ አንዱ ነበር።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.