Fana: At a Speed of Life!

ለአምራች ኢንተርፕራይዞች የብድር ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ 200 ሚሊየን ዶላር በጀት አለ- የአነስተኛና መካካለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር ድጋፍ የሚውልና ለ3 ዓመት የሚተገበር ተጨማሪ የ200 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት መኖሩን የአነስተኛና መካካለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት አስታወቀ፡፡
የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የመንዝወርቅ ግረፌ ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል በሊዝ ፋይናንስ፣ በስራ ማስኬጃና በንግድ ልማት አገልግሎት ኢንተርፕራይዞችን ሲደግፍ መቆየቱን ተናግረዋል። በነበረው አፈፃፀም ለተጨማሪ 3 ዓመት የሚተገበር የ200 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የብድር በጀት ማግኘቱን ነው ያስታወቁት።
ተጨማሪ የብድር ድጋፉ በልማት ባንክ፣ በንግድ ባንኮችና በማክሮ ፋይናንስ ተደራሽ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በኮቪድ-19 የተጎዳውን የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፍ ለማነቃቃት፣ ከጥቃቅን የተሸጋገሩ ሴት አምራቾችን ለመደገፍና ለኢንተርፕራይዞች የገበያ መረጃ በማቅረብና ለምርቶቻቸው የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ መልካም ዕድል ማምጣቱንም ነው ያብራሩት፡፡
ፕሮጀክቱ በአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ የሚገኙ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በማሽን ሊዝ፣ በስራ ማስኬጃና በንግድ ልማት አገልግሎት ተጠቃሚ ያደርጋል ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አስፋው አበበ ተናግረዋል፡፡
መንግስት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ውጤታማነት ለማሳደግ÷ በፋይናንስ፣ በመሰረተ ልማትና በጥሬ ዕቃ ግብዓት አቅርቦት፣ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት እንዲሁም በገበያ ትስስር እንዲደገፉ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
የፋይናንስ ፕሮጀክቱ ከልማት ባንክ ጋር በመተሳሰር የኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስና የንግድ ልማት አገልግሎት ችግር ለመፍታት በመጀመሪያው ምዕራፍ በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን÷ ለተጨማሪ 3 ዓመት የትግበራ በጀት መፈቀዱ ደግሞ የዘርፉን የፋይናንስ ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ ለመፍታትና ለመደገፍ መልካም ዕድል ይፈጥራል ማለታቸውን ከኢትዮጵያ ኢንተር ፕራይዝ ልማት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.