Fana: At a Speed of Life!

የህገ- መንግስት አጣሪ ጉባኤ እጩ አባላት እንዲሾሙ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ እጩ አባላት እንዲሾሙ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ጸደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ሶስተኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።
በህገ መንግስቱ መሰረት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅራቢነት በሪፐብሊኩ ኘሬዚዳንት የሚሾሙ በሙያ ብቃታቸውና በሥነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው ስድስት የሕግ ባለሙያዎች እንደሚሾሙ ይታወቃል።
ቀደም ሲል የተመረጡት አባላት የአገልግሎት ጊዜያቸው በሐምሌ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ተጠናቋል።
በመሆኑም በምክር ቤቱ በሙያ ብቃታቸው እና በስራ ልምዳቸው የቀረቡት እጩዎች በሪፐብሊኩ ኘሬዚዳንት የሚሾሙ በመሆኑ በዛሬው እለት በ4 ተቃውሞ በ12 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
የህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ 11 አባላት ሲሆኑ 6ቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚቀርቡ ናቸው።
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አሥራ አንድ አባላት ይኖሩታል፡፡
ጉባኤውን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት በሰብሳቢነት እንዲሁም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ኘሬዚዳንት በምክትል ሰብሳቢነት ይመሩታል።
ምክር ቤቱ እያካሄደ በሚገኘው መደበኛ ስብሰባ ለፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባልነት የቀረቡለትን ዕጩ የጉባኤ አባላት በ13 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር ዕይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ይጠበቃል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.