Fana: At a Speed of Life!

የጌዴኦ ዞን ነዋሪዎች ከ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አበረከቱ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዴኦ ዞን ነዋሪዎች ከ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ በገንዘብ የሚተመን ቁሳቁስ በአፋርና አማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ነው ድጋፍ ያደረጉት፡፡

ኢትዮጵያዊነት ማለት በደስታም ሆነ በሀዘን መረዳዳትና ያለን ተካፍሎ መኖር ነውና ወገኖቻችን በሜዳ ላይ ተበትነው የሚለብሱት የሚቀምሱት ሳይኖራቸው አይቶ ዝም የሚል አንጀት የለንም ካለን ላይ ብቻ ሳይሆን ያለንን አካፍለን እንለግሳለን፤ እኛ እያለን አይቸገሩም በማለት የተለያዩ ቁሳቁስ ለግሰዋል፡፡

ከአንድ ቤት አንድ ዕቃ በሚል መሪ ቃል በገንዘብ ሲተመን ከ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁስ አምጥተው ማስረከባቸውን የዞኑ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ እቴነሽ በየነ ገልፀዋል፡፡

ቡድኑ በአማራና በአፋር ክልሎች ያደረሰው አሰቃቂ ግፍና በደል በተለይም በሴቶችና ህፃናት ላይ ይህ ነው ተብሎ የማይገለፅ የስነልቦና ጉዳት ጭምር ማስከተሉ የማይካድ ሀቅ ነውና ይህንን ተግባር እያወገዝን ከወገኖቻችን ጎን እንቆማለን ብለዋል፡፡

ነዋሪዎች ለተፈናቃይ ወገኖች ለሚያርጉት ድጋፍ ያመሰገኑት ወይዘሮ እቴነሽ የተሰበሰበው ቁሳቁስ በዞኑ መንግስት አማካይኝነት ወደ ስፍራው እንደሚደርስ ተናግረው ድጋፉም ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በታሪክነሽ ሴታ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.