የሀገር ውስጥ ዜና

የሻሸመኔ ፋና ኤፍ ኤም 103 ነጥብ 4 ጣቢያና የነቀምቴ ፋና ኤፍ ኤም 96 ነጥብ 1 ጣቢያ ሰራተኞች ደም ለገሱ

By Feven Bishaw

December 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሻሸመኔ ፋና ኤፍ ኤም 103 ነጥብ 4 ጣቢያና የነቀምቴ ፋና ኤፍ ኤም 96 ነጥብ 1 ጣቢያ ሰራተኞች ደም በመለገስ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ህይወታቸውን ለህዝባቸው እየሰጠ ለሚገኘው ጀግናው መከላከያ ሰራዊት እኛ የምንሰጠው ደም አነስተኛ የበጎ አድራጎት ተግባር ነው ብለዋል።