Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ችግር ለመፍታት አቅሙና ጥበቡ ያላት አገር ናት – ዶ/ር በለጠ ሞላ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ውስጣዊ ችግር ለመፍታት አቅሙና ጥበቡ ያላት ሀገር ናት ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ተናገሩ።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከስዊድን አምባሳደር ሀንስ ሄነሪስ ሉንዱኪስት ጋር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና በሌሎች ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ስዊድን በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የዳበረ ልምድ ያላት አገር በመሆኗ ኢትዮጵያ ይህንን ልምድ መውሰድ እንደምትፈልግና ድጋፍም እንደምትሻ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ስዊድን በተለያዩ መስኮች ለኢትዮጵያ በምታደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ ÷ በ አይ ሲ ቲ እና ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ኢትዮጵያ ያለባትን የሰው ሀይል ክፍተት ለመሙላት ስዊድን ቀደም ሲል ስታደርግ የነበረውን ትብብርና ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሀንስ ሄነሪስ ሉንዱኪስት ÷ በቴክኖሎጂና ስራ ፈጠራ፣ በትምህርትና ግብርና ዘርፍ ኢትዮጵያን ለመደገፍ አገራቸው ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ ከ13 በላይ የስዊድን ኩባንያዎች እንዳሉ የገለፁት አምባሳደሩ ÷ አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ በስዊድን በኩል ያለውን ስጋት አንስተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ውስጣዊ ችግር ለመፍታት አቅሙና ጥበቡ ያላት አገር መሆኗን ለአምባሳደሩ ማረጋገጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.