Fana: At a Speed of Life!

የመንግሥት መ/ቤቶች በአፋር ክልል የወደሙ ፖሊስ ጣቢያዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ኢትዮ ቴሌኮም በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ ፖሊስ ጣቢያዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በአፋር ክልል ተገኝተው÷ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል፡፡

ድጋፉ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሲሆን÷ ተቋማቱ በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት የደረሰባቸው ፖሊስ ጣቢያዎችን ለማቋቋም የሚረዱ እንደ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ጠረጴዛ፣ ወንበር እና ሌሎች ለቢሮ ስራ የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ ፖሊስ ጣቢያዎቹ ወደስራ በመግባት የህብረተሰቡን ሰላም ለመመለስ እና በሽብር ቡድኑ የተፈፀሙ ወንጀሎችን አደራጅቶ ለመሰነድ እንደሚያግዝ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በአሸባሪው ህወሓት ከአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የ4 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ አስረክቧል፡፡

ድጋፉን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተወካይ በሰመራ ተገኝተው ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ አስረክበዋል።

ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ÷ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመው÷ በቀጣይ የፈረሱ የውሃ እና የመብራት መሰረተ ልማቶችን ዳግም በማቋቋም የጎርፍ መከላከል ተግባራትም ይሰራል ብለዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በተወካያቸው በኩል የ2 ነጥብ 5 ሚሊየን የአይነት ድጋፍ አስረክበዋል፡፡

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ÷ ለሰጣችሁን ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል።

ድጋፉ አልባሳት፣ ሩዝ፣ ፓስታ፣ ማካሮኒ እና የጽዳት መጠበቂያዎችን ያካተተነው፡፡

በበላይ ተስፋዬ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.