Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል መንግስት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል መንግስት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት ÷ በአሁኑ ወቅት አገር ለማዳን በሚደረገው ትግል በየደረጃው የሚገኘው የክልሉ አመራር የበኩሉን መወጣት አለበት ብለዋል።

አክለውም አመራሩ ከህልውና ዘመቻው ጎን ለጎን በክልሉ የሰፈነውን አስተማማኝ ሰላም እንዲጠናከርና የተከሰተውን ድርቅ አፋጣኝ መልስ ለመስጠት ከአመራሩ ብዙ ይጠበቃል ብለው፥ ለህዝብ የሚሰጠው አገልግሎትም አመራሩ ማጠናከር እንደሚኖርበት ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም አመራሩ ታች ወርዶ ከህዝቡ ጋር በቅንጅት በመስራት እየተካሄዱ ያሉትን ሥራዎች መጠናከር አለበት ብለዋል።

ክልሉ ከሌሎች አገራት ጋር የሚዋሰናቸውን ረዥም ድንበር ፀረ ሰላም ኃይሎች እንዳይገቡ ሌትና ቀን እየጠበቀ ያለውን የክልሉን ልዩ ሀይልና የፀጥታ አካላትን አመራሩ ማገዝ አለበት ብለዋል ።

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ በበኩላቸው፥ አገር ተገዳ የገባችው የህልውና ጉዳይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት ነው ብለዋል።

ከህልውና ዘመቻው ጎን ለጎን ልማትን በማፋጠን አመራሩ ብልጽግናን ማጠናከር እንዳለበት ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገነነው መረጃ ያመለክታል።

በሌላ በኩል በጠቅላይ ሚኒስትር አቅራቢነት የመሀልና የዳርና አጋር ሳይባል ሁሉን አካታች የሰላም የውይይት ማድረግ ለሚደረገው አገራዊ ንቅናቄዎች ድጋፋችንን እንገልፃለንም ነው ያሉት።

በውይይት መድረኩ ላይ አመራሩ ባቀረቡት አስተያየት የህልውና ዘመቻውን በተሳካ መልኩ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።

በሶማሌ ክልል ያለውን አስተማማኝ ሰላም ለማጠናከርና ለድርቁ ምላሽ ለመስጠትም ታች ድረስ በመውረድ በድርቅ ምክንያት የተጎዱትን ዜጎች ለመታደግ በሚደረገው ርብርብ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አስምረውበታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.