Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በደሴ እና ኮምቦልቻ በሚገኙ 40 ፋብሪካዎች ላይ ጉዳት አድርሷል – የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በደሴ እና ኮምቦልቻ በሚገኙ 40 ፋብሪካዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን በጥናት መረጋገጡን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ዛሬ በሰጡት መግለጫ ስምንት ፋብሪካዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም እነዚህ ፋብሪካዎች በአጭር ጊዜ እንደማይመለሱ ተናግረዋል፡፡

ስምንቱ ደግሞ መካከለኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ጠቅሰው፥ 24 የሚሆኑ ፋብሪካዎች ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፡፡

በቀላሉ ወደስራ የሚገቡትን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለሙያዎች ታግዞ ወደስራ ለማስገባት ስራዎች መጀመራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ጉዳት በደረሰባቸው 40 ፋብሪካዎች ውስጥ ከ11 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው እንደነበር አንስተው ÷ በአሁኑ ወቅት ግን ሰራተኞቹ ከእነቤተሰቦቻቸው ለእንግልት መዳረጋቸውን አስረድተዋል፡፡

ተግባሩ አሸባሪው ቡድን ለኢትዮጵያ ያለውን ጥላቻ ያሳየበት ጥግ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ፥ የዘረፉትን ሃብት የተመድ አርማ በተለጠፈባቸው መኪኖች ጭነው መውሰዳቸውን አስረድተዋል፡፡

ከእነሱ የተረፈውን ደግሞ ዜጎችን አስገድደው እንዲዘርፉ በማድረግ በካሜራ መቅረጻቸውን አንስተው፥ ይህም ‘’እኛ አልዘረፍንም’’ በማለት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማድረስ የተሰራ ስራ ነው ብለዋል ፡፡

ዘረፋው በከፍተኛ ባለሙያ የተደገፈ መሆኑን የተናገሩት አቶ መላኩ፥ በአጠቃላይ ፋብሪካዎቹ የተዘረፉ ቁሳቁስ በባለሙያዎች የተፈቱ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡

የባለሃብቶችም ይሁን የመንግስት ሃብትን መጠበቅ ለጸጥታ አካላት ብቻ የሚተው አለመሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይም ከባለሃብቶች እና ከመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር ቀጣይ ሰኞ ውይይት እንደሚደረግም አውስተዋል፡፡

በፈቲያ አብደላ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.