Fana: At a Speed of Life!

ከ200 በላይ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ከፌደራል ፖሊስ ጋር በቅንጅት ባደረገዉ ክትትልና ቁጥጥር ከ200 በላይ የሽያጭ መመዝገቢያዎች መሳሪያዎችን መያዙን በሚኒስቴሩ የታክስ ማጭበርበርና ምርመራ ዳይሬክተር ሲሳይ ገዙ አስታወቁ፡፡

የሽያጭ መመዝገቢያዎቹ የተያዙት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ ÷ በአንድ ህንጻ ውስጥ ተከማችተዉ ግዢና ሽያጭ በሌለበት ህገ ወጥ ቦታ መገኘታቸውንም አክለዉ ገልፀዋል፡፡

በዚህ ድርጊት የተሰማሩት እነዚህ አካላት ሃሰተኛ ደረሰኞችን ግብይት እንደተካሄደ አስመስለዉ በመቁረጥ የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን የሚጎዳና የንግድ ማጭበርበር መፈፀማቸዉን በመግለጫዉ ተነስቷል፡፡

በምርመራው ግኝቱ 90 በመቶ የሚሆኑት በአስመጭነት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ ÷ ከዚህ ውስጥ አለም አቀፍ ድርጅቶችም የሚገኙበት መሆኑን ተመላክቷል፡፡

እስካሁን በተደረገው የምርመራ ግኝት ዉስጥ 40 ባለቤት የሌላቸዉ የሽያጭ መመዝገቢያዎችን መለየት መቻሉንም ጭምር በምርመራዉ ታዉቋል፡፡

በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የታክስ እና ጉምሩክ ወንጀል ምርመራ ዳሬክተር አቶ ብርሃኑ አባተ በበኩላቸዉ ÷ ድርጊቱ በርካታ ተዋናዮች ያሉበትና በቀጣይ ሰፊ ምርመራ የሚያስፈልገዉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዚህም ተቆጣጣሪ አካላት ሃላፊነታቸዉን በሚገባ ከመወጣት አኳያ መታየት ያለበት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ መሰል ወንጀሎችን አስቀድሞ ለመከላከል ህብረተሰቡ የሚያደርገዉን ጥቆማ እና ትብብር አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ሃላፊዉ ማሳሰባቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.