Fana: At a Speed of Life!

የህወሃትን ኢ-ሰብአዊ ጥቃቶችእና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዙ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች እየተካሄዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሃት ቡድን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጽማቸውን ጥቃቶች እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዙ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች እየተካሄዱ ነው።
ህዝባዊ ሰልፎቹ በሰመራ፣ በባህርዳር፣ በሀዋሳ፣ በድሬዳዋ፣ በወላይታ ሶዶና ሌሎች ከተማሞች ነው እየተካሄዱ ያሉት።
አሸባሪው ህወሓት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በሴቶችና ህጻናት ላይ እየፈጸመ ያለውን ጾታዊ ጥቃት የሚቃወምና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በባህር ዳር ከተማ ሚሌኒየም አደባባይ እየተካሄደ ነው።
ሰልፈኞቹ “አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሴቶችና በህጻናት ላይ እያደረሰ ያለው ጾታዊ ጥቃት ይቁም! ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሴቶችና ሕጻናት ላይ በጥፋት ቡድኑ እየተፈጸመ ያለውን ጾታዊ ጥቃት ሊያወግዝ ይገባል! ፣ የውጭ ጣልቃ ገብነትን እንቃወማለን! ፣ በአሸባሪው ወራረው ቡድን ጥቃት የተፈጸመባቸው ሴቶችን በመደገፍ ሰብአዊነታችንን እናሳይ!” የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እያሰሙ ነው።
የሰልፉ ዓላማ አሸባሪው ህወሓት በአማራና አፋር ክልሎች ወረራ ከፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ በሴቶች፣ በህጻናት፣ በአረጋውያንና በአካል ጉዳተኞች ላይ እየፈጸመ ያለውን አሰቃቂ ግፍና በደል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ መሆነኑን የኢዜአ ዘገባ ያመልከታል።
በሰልፉ ላይ በባህር ዳር ከተማና በአካባቢው የሚገኙ የሴቶች አደረጃጀቶች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች ከጠዋቱ 1፡30 ጀምሮ ነው እተየሳተፉ ያሉት።
በተመሳሳይ በድሬዳዋ አስተዳደር “ለኢትዮጵያ ሰላም ይስፈን፤ በአሸባሪው ሕወሃት ቡድን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃት ይብቃ!” በሚል መሪ ቃል ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
ሰልፈኞቹ የሴቶች፣ ህፃናትና የልጃገረዶችን ጥቃት ለመከላከልና ለማስወገድ ሁላችንም ሀላፊነታችንን እንወጣ፣ ፆታ ተኮር ጥቃት ይብቃ ፣ዝም አንልም፣ የሴቶች ጥቃትን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም ይብቃ የሚሉ እንዲሁም በቃ የሚሉ መፈክሮች እያሰሙ ነው፡፡
በሰልፍ ስነ-ስርአቱ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ጥሩዬ አሰፌ መታደማቸውን ከአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሲዳማ ክልል በአሸባሪው ህወሃት ቡድን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃትን የሚቃወም ሰልፍ በክልሉ ባለፋት ጊዜያት በተለያዩ አካባቢዎች ሲከናወን የነበረ ሲሆን÷ በዛሬው እለት በሀዋሳ ከተማ የማጠቃለያ ዝግጅት ነው እየተካሄደ ያለው፡፡
በመርሃ ግብሩ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ ሀገርን ከጠላት በመጠበቁ ሂደት ሴቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን በመግለፅ ይህን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ጦርነቱ ያላለቀ በመሆኑን አሁንም ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመቆም ሀገራቸውን ከጠላት መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በተቃውሞ ሰልፋ ላይ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን የሚደረሰ ጥቃት ይቁም፣ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን ነን፣ አንድ አንድ የምዕራቡ አለም ሀገራት እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ ያንሱ የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እያሰሙ ነው፡፡
ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን በሴቶችና ህጻናት ላይ የፈጸመውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የሚያወግዝ ክልል አቀፍ የሴቶች ሰላማዊ ሰልፍ በወላይታ ሶዶ ከተማም ተካሂዷል።
ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን የፈጸማቸው አረመኔያዊ ድርጊቶችን በሚያወግዘው ሰልፍ ላይ የደቡብ ክልል ዋና አፈጉባኤ ፋጤ ሰርሞሎን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ ሴት አመራሮች ተገኝተዋል።
ሉዓላዊነታችንና ብሄራዊ ጥቅማችንን በተባበረ ክንድ ይከበራል፣ ሰላም ይስፈን፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰው ጥቃት ይቁም የሚሉ መፈክሮችን ሴት ሰልፈኛች አሰምተዋል።
የክልሉ ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ ገልጸው በሴቶችና ህጻናት ላይ እየደረሰ ያለወ ድርጊት መወገዝ እንደሚገባው ተናግረዋል።

በብርሃኑ በጋሻው፣ ጥላሁን ሁሴንና እዮናዳ እና በእዮናዳብ አንዱዓለም

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.