የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

December 17, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳሰ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አክንውሚ አዲሲና ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ በቀጣይ ስለሚኖረው የላቀ ሚና ዙሪያ መክረዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአፍሪካ ልማት ባንክ በበርካታ ዘርፎች የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የልማት አጋር መሆኑን አንስተዋል።

በግብርና፣ ትራንስፖርት፣ ኃይል እና ውኃ ልማት ዘርፍ ባንኩ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አንስተዋል።

በእነዚህ ዘርፎች ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ባለፉት ጊዜያት ድጋፍ ማድረጉን አውስተዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ባስቸጋሪ ወቅት ያሳለፈች ቢሆንም በተለይ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ተስፋ ያለው ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል።

በተለይ ሴቶችን ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት በበኩላቸው÷ ባንኩ አምስት ቀዳሚ ትኩረት ብሎ የለያቸው የልማት ፕሮጀክቶች እንዳሉ ማስታወሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከእነዚህ መካከል ኢትዮጵያ ከኬንያ የሚያስተሳስራት ፈጣን መንገድን 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በፋይናንስ እየደገፈ መሆኑን፣ በአዲስ አበባ ለቀበና ወንዝ ልማት ፕሮጀክት ከ400 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም በአብነት አንስተዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!