Fana: At a Speed of Life!

የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት መቀየር የሚቻለው በምኞት ብቻ ሳይሆን በእውቀትና በሳይንሳዊ ምርምር ነው-አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳሰ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት መቀየር የሚቻለው በምኞት ብቻ ሳይሆን በእውቀትና በሳይንሳዊ ምርምር መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።

አቶ ሽመልስ የአዳሜ ቱሉ ግብርና ምርምር ማእከልን የጎበኙ ሲሆን፥  የባቱ አሳ ምርምር ማዕከልንም መርቀዋል።

በምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ ከተማ የተገነባው የዓሳ ምርምርና የውሃ ብዝሃ ሕይወት ሥልጠና ማዕከል የዓሳ እርባታ ቦታን ያካተተ ሲሆን፥ የተገነባውም ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እንደሆነ ነው የተጠቆመው፡፡

የሥልጠና ማዕከሉ 140 የመኝታ ክፍሎችን እንዳካተተም ተገልጿል፡፡

አቶ ሽመልስ ማእከላቱ ግብርናን ለማዘመን የጀመሯቸውን አዳዲስ ስራዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በማእከላቱም የተጀመሩ የቡናና ሙዝ ምርጥ ዘር የማባዛት ቴክኖሎጂ፣ የአሳ ዝርያ ማራቢያ እና የእንስሳት ልማትና ምርምር ቴክኖሎጂና ተያያዥ ስራዎችን ነው የጎበኙት።

በዚህም ወቅት በማእከላቱ የተጀመሩ ስራዎች የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት ለመቀየር ወሳኝ መሆናቸውን ያነሱት አቶ ሽመልስ በስራዎቹ መደሰታቸውን ገልፀዋል።

በምርምር ማህበረሰቡ የታየው መነቃቃት ተጠናክሮ ቀጥሎ ከውጭ የሚገባው የምርምር ውጤችን ማስቀረት እንዲቻል በርትተው እንዲሰሩም አሳስበዋል።

የክልሉ መንግስትም ያልተቋረጠ ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል፤ መሰል ማእከላትም  እንዲስፋፉ ይሰራል ብለዋል።

 

በሀብታሙ ተክለስላሴ እና ዳግማዊ ዴክሲሳ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.