Fana: At a Speed of Life!

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለጀግኖች የሰራዊት አባላት ማዕድ አጋራ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በደብረ ብርሃን ከተማ ተገኝተው በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ጀግኖች የሰራዊት አባላት የምሳና ራት ማጋራት መርሀ ግብር አካሄዱ፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ብሔራዊ ቲያትር ባለሙያዎች የሙዚቃ ዝግጅት አቅርበዋል፡፡
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው መርሀ ግብር ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተገኝተው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሚኒስትሯ “እናንተ ለሀገር ውድ ዋጋ የከፈላችሁ የሰራዊት አባላት፤ ውድ ህይወታችሁን ለሀገር ክብር ስትሉ የከፈላችሁ ናችሁና ስለ ሀገርና ሰንደቅ ክብር ስትናገሩ በሙሉ ልብና በኩራት ነው” ብለዋል፡፡
አክለውም “የሰራችሁት ስራ የውስጥና የውጭ ጠላትን አንገት ያስደፋ፥ ኢትዮጵያውያንን ቀና ያደረገ ስራ ስለሆነ እንኮራባችኋለን” በማለት ገልፀዋል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አስቴር ተክሌ በበኩላቸው÷ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች ከዚህ በፊት ለመከላከያ ሰራዊቱና ለተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውሰው፥ ለሰራዊቱ ከተሰጡት ሰንጋዎች ውስጥ ለሰራዊቱ ምሳና ራት በማዘጋጀት ምገባ ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲህ ዓይነት የምገባ መርሀ ግብር ሲያካሂድ ለ2ኛ ጊዜ መሆኑም ገልጸዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.