Fana: At a Speed of Life!

ቻይና አዲስ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአራት ሳምታት ውስጥ መቆጣጠር እንደምትችል አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና አዲስ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በ 4 ወር ውስጥ መቆጣጠር እንደምትችል የሃገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡
በሻንጋይ የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያ የሆኑት ዣንግ ዌንሆንግ እንደተናገሩት ÷ ቻይና በሀገሪቱ “ዜሮ ኮቪድ ፖሊሲ” መሰረት አንደ አዲስ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአራት ሳምታት ውስጥ እንደምትቆጣጠር አስታውቀዋል፡፡
“ቫይረሱን ማሸነፍ ለእኛ የጊዜ ጉዳይ ነው፥ መሸበር አያስፈልግም” ብለዋል ባለሙያው፡፡
አክለውም የቻይና ሳይንቲስቶች የኦሚክሮን ቫይረስ የተህዋሲ ባህሪ ልዩነት በሚያሳይበት ወቅት በፍጥነት ምላሽ መስጠታቸውን እና ከሁለት እስከ ሦስት ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ አዲሱን የተህዋሲ ልዩነት ለመዋጋት የሚያስችሉ ምርምሮችን ማድረግ መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡
የቻይና “ዜሮ ኮቪድ ፖሊሲ” የሀገሪቱ አጠቃላይ የኮቪድ-19 መከላከል እና ቁጥጥር መመሪያ ሲሆን፥ ይህም አዳዲስ ወረርሽኞች ሲከሰቱም በፍጥነት ለማጥፋት የሚወሰዱ እርምጃዎችን ያቀፈ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ፖሊሲው በአሁኑ ጊዜ እጅግ በጣም ወሳኝ የህዝብ ጤና መጠበቂያ ስትራቴጂ ነው ያሉት ባለሙያው፥ ቻይናበተለያዩ ግዛቶቿ በአዲስ መልክ የተከሰቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኞችን መቆጣጠር እንዳስቻላት ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አመላክቷል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.