Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ለአፋር ክልል አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ ሶስት የህክምና ተቋማትን መልሶ ለመቋቋም የሚያስችል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
 
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት በተለይም በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ ተቋማትን መልሶ መገንባትና ስራ ማስጀመር ዋነኛ ስራችን ሊሆን ይገባል።
 
ከዚያ አንፃርም ሐክልል በአፋር ክልል የወደሙ የጤና ተቋማት መልሶ ለማቋቋምና ስራ ለማስጀመር እየሰራ ይገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በእለቱም የወደሙ ሶስት የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
 
በቀጣይም ቁልፍ አጀንዳችን ሊሆን የሚገባው የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ስለማቋቋምና የወደሙ ተቋማትን ስራ ማስጀመር እንዲሁም ለህብረተሰቡ ከቀድሞው የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል መረባረብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
 
የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ኢብሳ ሙሳ በበኩላቸው፥ ክልሉ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው ደረጃቸውን የጠበቁ የህክምና ቁሳቁስ ለአፋር ክልል ድጋፍ አድርጓል።
 
የተደረገው ድጋፍ ዘመናዊ አልጋዎች፣ የማዋለጃ ቁሳቁስ፣ ማይክሮስኮፖች፣የቀዶ ጥገና መሳሪያዎች፣ ዊልቸር፣ ክራንች እና ሌሎች ቁሳቁስ መሆኑን ከሐረሪ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.