Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ ከሐገር ሽማግሌዎችና ከጎሳ መሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ ከክልሉ ሀገር ሽማግሌዎችና ከጎሳ መሪዎች ጋር በወቅታዊ ሐገራዊ ጉዳይ እና በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ዛሬ በጅግጅጋ ተወያይተዋል።
 
በውይይቱም ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የሶማሌ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ እና የጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙበሽር ዱበድ ተገኝተዋል።
 
አሁን ላይ እንደ የክልሉ መሪ ፓርቲና መንግስት ክልሉ ከአጎራባች ሐገራት ድንበር እንደ መዋሰኑ መጠን የአልሸባብን እና መሰል ሃይሎችን እንቅስቃሴ የመመከትና ሰፊ የጸጥታ ስራን በመስራት የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ያረጋግጣል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
 
በዚህም በማንኛውም ክልላዊና ሐገራዊ ጉዳዮች ላይ የሐገር ሽማግሌዎች የጎሳ መሪዎችና የእምነት አባቶች ያላቸው ቀና ተሳትፎ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እንደሆነ በአፅንኦት ገልጸዋል።
 
የሶማሌ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ በበኩላቸው፥ አሸባሪው ህወሓት ባለፉት ሁለት ሳምንታት በወገን ጥምር ጦር በከፍተኛ ሁኔታ ተመቶ ከበርካታ አካባቢዎች መውጣቱንና ድል መገኘቱን ጠቁመው÷ ቡድኑ ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ላይ መሆኑን አብራርተዋል።
 
እንደ ክልል በዝናብ እጥረት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የክልሉ መንግስት በደረቅ ሬሽን በንጹህ መጠጥ ውሐና የእንስሳት መኖዎችን እያደረሰ መሆኑን ጠቅሰው÷ጉዳቱ ካለው ስፋት አንፃርም ሁሉም ህዝብ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
 
በውውይቱ ላይ የተሳተፉ የሐገር ሽማግሌዎች የጎሳ መሪዎችና የሃይማኖት አባቶችም ከለውጡ ጀምሮ እንደ ክልል መንግስት በወቅታዊና ሐገራዊ ጉዳዮች ላይ አብሮ መወያየት መፍቀዱ አዲስና የሚመሰገን እንደሆነ መናገራቸውን የሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል።
 
በሐገሪቱ ላይ አደጋ ደቅኖ በነበረው አሸባሪ ቡድን ላይ እየተወሰደ ባለው የማያዳግም እርምጃ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘመቻ መደሰታቸውንም ገልጸዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.