Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ሺህ 400 በላይ የክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ በተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ ከ1 ሺህ 400 በላይ የክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ጥይት በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን ገለፀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ለፖሊስ አባላቱ 800 ሺህ ብር መደለያ እንስጣችሁ ቢሉም የፖሊስ አባላቱ መደለያውን ወደ ጎን በመተው ተጠርጣሪዎቹን ለህግ ማቅረባቸውንም አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ዛሬ በግምት ከጠዋቱ 3 ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ሰባተኛ ሆቴል አካባቢ ነው።

ግለሰቦቹ ለሽብር ተልዕኮ ማስፈፀሚያ የሚውሉ 1 ሺህ 461 የክላሽን- ኮቭ ጠብመንጃ ጥይቶችን በሱዙኪ መኪና ጭነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 3 ተጠርጣሪዎች ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ከእነ ተሽከርካሪው ሊያዙ መቻላቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም 57 ሺህ ብር፣ የራሳቸው ያልሆነ የቀበሌ መታወቂያ እና ፓስፖርት መያዙን እና በግለሰቦቹ ላይ አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።

በገንዘባቸው ተማምነው ህገ-ወጥ ተግባራትንና ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦችንም ህዝቡ አጋልጦ በመስጠት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.