የሀገር ውስጥ ዜና

መንግስት ለሀገር ውስጥ መድሃኒት አምራች ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግ ቁርጠኛ ነው – ዶ/ር ሊያ ታደሰ

By Feven Bishaw

December 17, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ እና የኢትዮጵያ መድሃኒት እና የህክምና ቁሳቁሶች አምራች ማህበራት በዛሬው ዕለት ጥራት ያለው የመድሃኒት አቅርቦት በተፈለገው ጊዜ ለዜጎች ለማድረስ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነት ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፥መንግስት ሀገር በቀል አምራች ኢንዱስትሪዎችን የማበረታት እና የማሳደግ ስራ ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡