የሀገር ውስጥ ዜና

ጀርመን ለኢትዮጵያ የ80 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ እርዳታ እንደምትሰጥ ይፋ አደረገች

By Meseret Awoke

December 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመን ለኢትዮጵያ የ80 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ እርዳታ እንደምትሰጥ ይፋ አደረገች፡፡

የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስቴር አቶ አህመድ ሺዴ ትናንት ታህሳስ 8 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደርን አውር ስቴፓንን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በዚህም ወቅት በሁለቱ አገራት የኢኮኖሚ ልማት ትብብር ላይ የተወያዩ ሲሆን ÷ አምባሰደሩ ጀርመን ለኢትዮጵያ የ80 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንደምታደርግ ይፋ አድርገዋል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው የምግብ ዋስትና ፕሮግራም፣ ለመልካም አስተዳደር፣ ለመሬት አጠቃቀም፣ ለግብርና ሜካናይዜሽን እንዲሁም ድርቅን ለመቋቋም ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች የሚውል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!