Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካዊያንን በማሳተፍ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የውጭ ጣልቃገብነት ለማስቆም እየተሠራ መሆኑ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “አፍሪካዊያንን በማሳተፍ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የውጭ ጣልቃገብነት ለማስቆም እየሠራን ነው” ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባልና የዩናይትድ ሚዲያ ሃውስ መስራች በኃይሉ መሃመድ ገለጹ።

በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ በተባበረ ክንድ እየመከቱት ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣው ዘመቻ ዘርፈ ብዙ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሁሉም ግንባሮች ተሰልፈው የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እያበረከቱ ነው፡፡

በውጭ ሀገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን የተጀመረው የ”#በቃ” ዘመቻ ደግሞ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ሲሆን ÷ አፍሪካዊያንና ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች ዘመቻውን በስፋት እየተቀላቀሉ ይገኛሉ፡፡

በደቡብ አፍሪካ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባልና የዩናይትድ ሚዲያ ሃውስ መስራች የሆኑት በኃይሉ መሃመድ ለኢዜአ እንደገለጹት ÷ ኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ለመመከት ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ እየሰራ ነው፡፡

በደቡብ አፍሪካና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን የውጭ ጣልቃ-ገብነት በሚመለከት ለአፍሪካዊያን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ሲያከናወኑ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡

በቅርቡም በደቡብ አፍሪካ የተባበሩት የኢትዮጵያዊያን ማኅበረሰብ ማኅበር ከአፍሪካ ዳያስፖራ ፎረም ጋር በመተባበር ከገንዘብ መዋጮ ጀምሮ ሀገራቸውን ለመደገፍ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ መሆኑን አንስተዋል።

ከሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉበት የ”#በቃ” ዘመቻ አካል የሆነ ሠላማዊ ሰልፍ በሀገሪቱ መዲና ፕሪቶሪያ መካሄዱንም ገልጸዋል፡፡

በሰልፉ “የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካዊያን ይፈታል” የሚለውን እሳቤ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልጸው ÷ ለዚህ ደግሞ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ላደረገላቸው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አፍሪካዊያንን በማሳተፍ ዘመቻው ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያን ህልውና ለማስቀጠል በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በቁርጠኝነት እየሠሩ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡

በዚህም በደቡብ አፍሪካና ደቡባዊ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሀገሪቱ ባሉ ስመ-ጥር መገናኛ ብዙኃን በመቅረብ በሀገራቸው ያለውን እውነት እያሳወቁ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ዳያስፖራው በአሸባሪው ህወሓት ወረራ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት ረገድ የበኩሉን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.