Fana: At a Speed of Life!

የዳግማዊ ምኒልክ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአሸባሪው ህወሓት ለወደመው የመሃል ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳግማዊ ምኒልክ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ለወደመው የመሃል ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የዳግማዊ ምኒልክ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ታደሰ ሃብተዮሐንስ፥ ሆስፒታሉን ሊያስጀምር የሚችል የአልትራሳውንድ፣ ፍሪጅ፣ ኦክስጅን፣ ልዩ ልዩ መድሃኒቶች፣ ለቀዶ ጥገና የሚያገለግሉ ማሽኖች፣ እንዲሁም አልጋዎችና ፍራሾች ተበርክተዋል ብለዋል፡፡

ይህ የመጀመሪያው ዙር ድጋፋችን ነው ያሉት ስራ አስኪያጁ፥ በቀጣይም ለሆስፒታሉ የምናደርገውን ድጋፍ እናስቀጥላለን ብለዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የመሃል ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ወርቅነህ ዘውዴ፥ ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው የሆስፒታሉ አገልግሎት በተረከብናቸው ቁሳቁሶች ይጀመራል ብለዋል፡፡

በአሸባሪው የጥፋት ቡድን የወደመውና የተዘረፈው የመሃል ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል በአካባቢው ለሚገኙ ከ 400 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር መገለጹን የመንዝ ገራምድር ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.