Fana: At a Speed of Life!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 486 የጤና ባለሙያዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለሁለተኛ ጊዜ 486 የጤና ባለሙያዎችን ዛሬ አስመርቋል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በ2022 ዓ.ም ቴክኖሎጂ መር የጤና ልህቀት ማዕከል የመሆን ራዕይ አልሞ እየሰራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ተናግረዋል፡፡
የዘንድሮውን ምረቃ ለየት የሚያደርገው÷ የሀገርን ሠላም ለማስከበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስከ ግንባር በመዝመት በብቁ ወታደራዊ አመራር የውስጥና የውጭ ጠላቶችን አንገት ያስደፉበት ወቅት መሆኑ ነው ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው ለሀገር ህልውና ላበረከተው አስተዋጽኦ ያመሰገኑት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢና የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አክሊሉ ለማ÷ በተመራቂዎች የትምህርት ሕይወት ምዕራፍ ላይ የመምህራን ሚና የላቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ኦቶና ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር ሉቃስ ዲንጋቶ ÷ ለመከላከያ ሠራዊት ደጀንነት ማሳያ እንዲሆን የሆስፒታሉ አጠቃላይ ሠራተኞች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ተመራቂዎች በበኩላቸው በሙያችን ሰርተን ለመብላት የአገር ሠላም ወሳኝ በመሆኑ÷ ቅድሚያ ሀገር በምትፈልገን መስክ ሁሉ የሚጠበቅብንን ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ለ13ኛ ጊዜ ነው ያስመረቀው፡፡
በአበበች ኬሻሞ እና መለሰ ታደለ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.