Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንድታገኝ የተጀመረው እንቅስቃሴ የፍትህ፣ እኩል የመሆንና የነጻነት ትግል ነው – ዶ/ር መሃመድ ሃሰን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካን ተጽእኖ ፈጣሪ ለማድረግ በጋራ መቆም አማራጭ የሌለው መንገድ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና እስያ ጥናት ምርምር ተቋም መምህር ዶክተር መሃመድ ሃሰን ተናገሩ።
አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ኢትዮጵያ ያራመደችውን ጽኑ አቋም ሁሉም የአፍሪካ አገራት አጀንዳቸው አድርገው ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ጠቁመው÷ የአፍሪካውያን በጋራ መቆም ተሰሚነታቸውንና ተጽእኖ ፈጣሪነታቸውን ለማሳደግ ሁነኛ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ማግኘት አለባት የሚለውን ትግል መቀላቀላቸውን መግለጻቸው በሌሎች የአፍሪካ አገራት ዘንድ መነቃቃትን መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንድታገኝ የተጀመረው እንቅስቃሴ የፍትህ፣ እኩል የመሆን እና የነጻነት ትግል በመሆኑ ሁሉም አፍሪካውያን ድምጻቸውን አጉልተው ማሰማት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻነት እንዲረጋገጥ በሄደችበት መንገድ ዛሬም ይህ ጥያቄ በእሷ በኩል መነሳቱ ትግሏ የመላ አፍሪካውያን ትግል ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.