Fana: At a Speed of Life!

በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃትን የሚቃወም ሰልፍ ነገ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሰላም ይስፈን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም” በሚል መሪቃል ነገ ታህሳስ 10 ቀን 2014 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ህዝባዊ ሰልፍ ይካሄዳል፡፡
መርሃ ግብሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል፡፡
በዚሁ መሠረት ፡-
• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ እና ታች መንገዶች
• ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ላይ እና ታች መንገዶች
• ከ4 ኪሎ በውጪ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሄራዊ- ቤተ መንግስት
• ከአዋሬ ካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ መብራት
• ከሜክሲኮ፣ለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር ትራፊክ መብራት ላይ
• ከሰንጋ ተራ ብሄራዊ ቴአትር ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት
• በቸርችል ጎዳና ፖስታ ቤት፣ ሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ መብራት
• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ እና ለቀላል ተሸከርካሪ ጥላሁን አደባባይ ዝግ ይሆናል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ዙሪያ እና በእነዚህ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።
አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ የጠየቀው ፖሊስ÷ በተለይም ወቅታዊውን የሀገራችንን የፀጥታ ሁኔታ ከግምት በማስገባት የከተማችን ነዋሪዎች ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሲል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል ፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.