በኦሮሚያ ክልል በ12 ዞኖች የኩፍኝ በሽታን ለመቆጣጠር እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ12 ዞኖች የኩፍኝ በሽታን ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ገለፀ።
በክልሉ በ12 ዞኖች በሚገኙ 58 ወረዳዎች የኩፍኝ በሽታ መታየቱን ቢሮው አስታውቋል።
ባለፉት ስድስት ወራት ከስድስት ሺህ በላይ ህፃናት በወረርሽኙ ተይዘው በጤና ተቋማት ክትትል ተደርጎላቸዋል።
በአሁኑ ወቅትም በ14 ወረዳዎች የተፈጠረውን የኩፍኝ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።
የኩፍኝ በሽታ ምልክቶች ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት፣ ነጠብጣብ የሚመስሉ ምልክቶች በቆዳ ላይ በሽፍታ መልክ መታየት፣ የዓይን መቅላት፣ በአፍንጫ የሚወጣ ከፍተኛ ፈሳሽ፥ ቤተሰብ እነዚህን ምልክቶች በህፃናት ላይ ሲያይ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋማት እንዲወስድ ቢሮው አሳስቧል።
አሁን ላይም የህክምና ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች በሽታው ወደ ታየባቸው አካባቢዎች ተሰማርተዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision