Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ማጣቷ ታላቅ ኢ-ፍትሐዊነት ነው – ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይፕ ኤርዶኻን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ሕዝብ ያላት አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ማጣቷ እና መምረጥ አለመቻሏ ታላቅ ኢ-ፍትሐዊነት ነው ሲሉ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይፕ ኤርዶኻን ተናገሩ።
አፍሪካ በዚህ ምክር ቤት በሚገባት መልኩ ውክልና እንድታገኝ ሁላችንም በትብብር መሥራት ይጠበቅብናል የሚል እምነት አለኝ ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
ከተለመደው አሠራር ተጠቃሚ የሆኑ አካላት በጥረታችን ቢያኮርፉንም እንኳ ለልጆቻችን መፃኢ ጊዜ ስንል ይህንን ትግል ለመጀመር ቁርጠኞች ነን ሲሉም አሳውቀዋል።
የሰው ዘር ሁሉ ዕጣ ፈንታ በአምስቱ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት ብቻ እጅ ላይ መውደቁ ትክክል እንዳልሆነ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያሳለፍናቸው ክስተቶች በግልጽ አሳይተውናል ነው ያሉት ረጀብ ጣይፕ ኤርዶኻን።
አፍሪካ በምክር ቤቱ ተገቢውን ውክልና እንድታገኝም ቱርክ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ለአፍሪካ ያላትን አጋርነት ታረጋግጣለች ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቱርክ የአፍሪካ ሀገራት ለነጻነታቸው በሚያደርጉት ማንኛውም ትግል ላይ ድጋፍ ታደርጋለች ሲሉ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.