Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከቱርክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከቱርክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሳዳት ኦናት ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
አምባሳደር ሬድዋን÷ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም መንግስት ግጭቱን ለማስቀረት ያደረገውን ጥረት እና በግጭቱ ምክንያት ተጎጂ ለሆኑ ወገኖች ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት እንዲኖር እየተደረገ ያለውን ጥረት አብራርተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለው ግጭት ተስፋፍቶ መቀጠል ከህወሃት ግጭት ናፋቂ ባህሪይ የመነጨ ስለመሆኑም ጨምረው ገልጸዋል።
ሁሉን አሳታፊ የሆነ ብሔራዊ የምክክር መድረክ ለማካሄድ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት የተጠናቀቀ ስለመሆኑም አስረድተዋቸዋል።
የቱርኩ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰአዳት ኦናት በበኩላቸው÷ ግጭቱን በማስቆም የተኩስ አቁም እርምጃ ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልበት አማራጭ እንዲታይ ጠይቀው÷ አገራቸው በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት የሚደረገውን የሰላም ጥረት የምትደግፍ መሆኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ እና ቱርክ መካከል በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እና አቅም ግንባታ ዘርፎች የሚደረጉ የጋራ ትብብሮችን በተመለከተም ውይይት መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.