Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ ፓርላማ በህዝብ ድምፅ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ ህዝብን ድምጽ እንዲያከብር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፓርላማ በዲሞክራሲያዊ መንገድ በህዝብ ድምፅ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግስት እና የኢትዮጵያን ህዝብ ድምጽ እንዲያከብር ተጠየቀ፡፡

ድፌንድ ኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ግብረሀይል የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በለንደን የፓርላማ አደባባይ የእንደራሴዎቹ የአመቱ የፓርላማ ስብሰባ ማጠናቀቂያ ላይ ተካሂዷል፡፡

በሰልፉ ተቃውሟቸውን ያሰሙት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን÷ የእንግሊዝ ፓርላማ በዲሞክራሲያዊ መንገድ በህዝብ ድምጽ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግስት ከሽብርተኛው ቡድን ጋር እኩል መቆጠሩ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ኪንግደም እንደራሴዎች አሸባሪውን ቡድን በመደገፍ በዲሞክራሲያዊ  መንገድ በተመረጠው  የኢትዮጵያ መንግስት ላይ  ጫና ለማሳረፍ በእኛ በመራጮቻችሁ ስም የምታደደርጉት ስብሰባ እጅግ ያሳዝናል ብለዋል፡፡

ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና ለነጻነት ወዳጅ የሆነችውን ኢትዮጵያ  እና መንግስቷ ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር የአፍሪካ ቀንድን ለማፍረሥ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት የለውም ብለዋል ሰልፈኞቹ፡፡

እንደራሴዎቹ ከቻሉ የኢትዮጵያን መንግስት በመደገፍ አብረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡

ከዚህ በኋላ  በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ላይ ጫና በማሳደር መቀጠል አይቻልም ያሉት ሰልፈኞቹ÷ ኢትዮጵያ በህዝቦቿ ጥረት እና አቅም ሁሉንም ጫና ተቋቁማ በእግሯ እንደምትቆም አረጋግጠዋል፡፡

ሰልፈኞቹ በእንግሊዝ ፓርላማ ተወካይ እንዲሆኑ ድምጽ የሰጧቸውን እንደራሴዎች በየግል ጽህፈት ቤታቸው በመገኘት እንደሚያነጋግሩ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.