Fana: At a Speed of Life!

በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚሆን ድጋፍ አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በአሸባሪው ህወሓት ወረራ የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ 10 ሺህ 370 ፓውንድ ለገሱ።
ገንዘቡን የተቀበሉት በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ÷ በስቶክ ኦን -ትሬንት የሚገኘውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አመስግነው፤ በዚህ አስጨናቂ ወቅት ለትግሉ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።
አምባሳደሩ በዓለም ዙሪያ ያሉ የዳያስፖራ ማህበረሰብ ከኢትዮጵያ ጋር እንዲቆሙ እና የእናት ሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ እንዲደግፉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.